-
የኢንተርኘራይዞችንና የኢንደስትሪ ልማት ለማፋጠን የሚረዱ ተቋማዊ ስትራቴጂዎች፣ ስልቶችን፣ ፕሮግራሞችን፣ ፕሮጀክቶችን፣ የድጋፍ ማዕቀፎች፣ መመሪያዎችንና እቅዶችን ያዘጋጃል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፤
የኢንተርኘራይዞችና ኢንደስትሪዎች የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎችን ያቋቁማል፣ ያስተባብራል፣ ይቆጣጠራል፤
ኢንተርኘራይዞችና አምራች ኢንደስትሪዎችን በንግድ ህጉ እና አግባብ ባለው ሌላ ህግ መሰረት ያደራጃል፤ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፤
በኢንተርኘራይዝና ኢንደስትሪ ልማት ለተሰማሩ አንቀሳቃሾችና አምራቾች የሙያ ማበልፀጊያ ስልጠናዎች እና አውደ ርዕዮች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፤
ኢንተርኘራይዞችና አምራች ኢንደስትሪዎች የመረጃ፣ የቴክኖሎጂ መረጣ፣ የድርድር፣ የግንባታ፣ የኮሚሺኒንግ ድጋፍ ይሰጣል፤ ውጤቱንም ይገመግማል፤
ለኢንተርኘራይዞችና አምራች ኢንደስትሪዎች የመረጃና የምክር አገልግሎት የሚሰጥበት የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፤ ተፈጻሚነቱን ይከታተላል፤
የኢንተርኘራይዞችና አምራች ኢንደስትሪዎች የብቃት ማረጋገጫ እንዲሁም የደረጃ እና የጥራት ሰርቲፊኬሽን እንዲያገኙ ድጋፍ ያደርጋል፤
ኢንተርኘራይዞችንና አምራች ኢንደስትሪዎች ከጥቃቅን ወደ አነስተኛ፤ ከአነስተኛ ወደ መካከለኛና ከመካከለኛ ወደ ከፍተኛ የዕድገት ደረጃ እንዲሸጋገሩ ያደርጋል፤
ኢንተርኘራይዞችና አምራች ኢንደስትሪዎች ተወዳዳሪ ለማድረግ በጥናት ላይ የተመሰረተ የማበረታቻ፣ የዕውቅና እና ሽልማት ስርዓት ይዘረጋል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፤
የኢንተርኘራይዞችና አምራች ኢንደስትሪዎች በዘርፍ ማህበራት ያደራጃል፤ ውጤታማ እንዲሆኑ አስፈላጊውን እገዛ ያደርጋል፤
የመስሪያና መሸጫ ቦታዎች፣ ክላስተር ማዕከላትንና ኢንፖሪየሞችን በክላስተር ፅንሰ ሀሳብ መሰረት ዲዛይን እንዲዘጋጅ በማድረግ ማሰገንባት፣
ሥራና ሠራተኛ ለሚያገናኙ ኤጀንሲዎች የብቃት ማረጋገጫ በህግ መሰረት ይሰጣል፤ ድጋፍ ያደርጋል፤ መሥራታቸውን ያረጋግጣል፤ ይሰርዛል፤
ሥራና ሠራተኛ ለሚያገናኙ ኤጀንሲዎች እና የግል የስራ ሁኔታ ቁጥጥር አገልግሎት አቅራቢዎች የብቃት ማረጋገጫ መስጠት፤
ስለውጭ አገር ሥራ ስምሪት እና ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር የግንዛቤ ማሳደጊያ ሥራዎችን መስራት፤
ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች
- የሥራ ስምሪት በማስፋፋት የስራ ዕድል መፍጠር
- ለኢንዱስትሪ ልማት መሰረት የሚጥል ዘርፍ እንዲሆን ማስቻል፣
- በከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ተጠቃሚ ማድረግ
- የመስሪያ ቦታ ልማትና አቅርቦት
- ምቹ የሥራ ቦታና አካባቢ መፍጠር