በልደታ ክ/ከተማ የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስቱሪ ልማት ጽ/ቤት የተከናወኑ ስራዎች ዜና
በልደታ ክ/ከተማ የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስቱሪ ልማት ጽ/ቤት የተከናወኑ ስራዎችን በፎቶ
በልደታ ክ/ከተማ የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስቱሪ ልማት ጽ/ቤት የተከናወኑ ስራዎች በቪዲዮ
በልደታ ክ/ከተማ የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስቱሪ ልማት ጽ/ቤት መግለጫዎች
በልደታ ክ/ከተማ "ኢትዮጲያ ታምርት" በሚል መሪ ቃል ከአምራች ኢንዱስትሪዎች ጋር ምክክር ተደርጓል። በፕሮግራሙ ሪፖርት ያቀረቡት የስራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ ጌታሁን ሀይለማሪያም እንደተናገሩት አምራች ኢንዱስትሪዎችን በመደገፍና በማበረታታት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካትና ወደ ውጭም ኤክስፖርት የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው ሲሉ ገልፀዋል።
አቶ ጌታሁን አክለውም በ1ኛው ኢትዮጲያ ታምርት ንቅናቄ ኢንዱስትሪዎች ሲያነሷቸው የነበሩ ችግሮችን በመቅረፍ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ተችሏል ሲሉ ገልፀዋል።
በልደታ ክ/ከተማ የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች ያመረቷቸውን ምርቶች ለእይታ በማቅረብ ማህበረሰቡ በሀገር ምርት እንዲኮራ የሚያስችል ግንዛቤ ፈጥረዋል።