አገራችን ኢትዮጵያ የበለጸገችና መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ በማሰለፍ የህዝቧን የኑሮ ሁኔታ ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማሻሻል የሚያስችል መዋቅራዊ አደረጃጀት በመፍጠር ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ሀገራዊ የድህነት ቅነሳ ግብን ለማሳካት ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡ በክ/ከተማችን የአስተዳደሩን ትኩረት የሚሹ እና በተደራጀ የልማት እና መልካም አስተዳዳር ዕቅድ ምላሽን የሚጠይቁ በርካታ ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ችግሮች በመኖራቸውና የጥቃቅን ፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ለኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ዕድገት በተለይ ለኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂ ትግበራ መሳካት ያለውን ፋይዳ ግምት ውስጥ በማስገባት ከመቸውም ጊዜ በላይ በበቂ አካላዊ እና ስነልቦናዊ ዝግጅት ወደ ትግበራ ገብተናል፡፡
የልደታ ክ/ከተማ ም/ስራ አስፈጻሚ እና
የስ/ኢ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ኀላፊ