|
|
የክፍለ ከተማው የመስሪያ ቦታ አስተዳደር ስልጣንና ተግባር፡-
|
|
- የመስሪያ ቦታ ድጋፍ የሚገባቸውን ኢንተርፕራይዞች መረጃ ትክክለኛ መሆኑን አረጋግጦ በተቀመጠው አሰራር ሥርዓት መሠረት የኤጀንሲውን ውሳኔ ያስፈጽማል፡፡
- አዲስ ተመልምሎ ወደ ክላስተር ማዕከላት (ህንጻዎች) የሚገቡ የቦታ ስፋታቸው እስከ 120 ካ.ሜ እና የቦታ ስፋታቸው እስከ 240 ካ.ሜ በሆኑ ሼድ የሚመደቡ ኢንተረፕራይዞችን በተመለከተ በወጣው መስፈርት መሰረት ተገምግሞ በክ/ከተማው ፕሮሰስ ካውንስል ውሳኔ ይሰጣል፡፡
- ስፋታቸው እስከ 50 ካሬ የሆነ በኢንተርፕራይዞች የሚቀርበውን የማስፋፈያ ጥያቄዎች ላይ በመመሪያው መሰረት አስፈላጊውን ውሳኔ በፕሮሰስ ካውንስል በመወሰንና በመስጠት ሪፖርት ለኤጀንሲው ያቀርባል፡፡
- የመስሪያ ቦታ ተጠቃሚ ኢንተርፕራይዞች ሙሉ መረጃ ቀልጣፋና ዘመናዊ በሆነ መንገድ ወደ መረጃ ቋት አስገብቶ ይይዛል፡፡
- የመስሪያ ቦታ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተወሰነላቸውን ኢንተርፕራይዞች መለያ ቁጥር በመስጠት እንደቅደም ተከተላቸው ውል እንዲዋዋሉ ያደርጋል፣ ይከታተላል፡፡
- በሕገ-ወጥ መንገድ የተያዘ የመስሪያ ቦታ በቀረበው መረጃ መሰረት እርምጃ ይወስዳል፣ የውሳኔ ሐሳብ ለሚመለከተው ያቀርባል፣ድጋፍ ያደርጋል፡፡
- የመስሪያ ቦታዎች ለታለመላቸው ዓላማ ስለመዋላቸው ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፡፡
- የከተማው ነዋሪ ሆነው አዕምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት የስራ ፈጠራ ባለቤትነት ሰርተፍኬት መብት ይዘው የሚቀርቡና ፈጠራቸው ቢተገበር የስራ ዕድል እንደሚፈጥር የታመነበትን የመስሪያ ቦታ ፈላጊዎች በአንዱ የፈጠራ ስራ ዘርፍ ብቻ በኤጀንሲው ውሳኔ መሰረት አሰራሩን ተከትሎ ያስፈጽማል፡፡
- በመመሪያው ከተጠቀሱት የስራ ዘርፎች ውጪ የመስሪያ ቦታ ጥያቄ ሲቀርብ ኤጀንሲው በሚሰጠው ውሳኔ መሰረት አሰራሩን ተከትሎ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
- መስሪያ ቦታን በሚመለከት ለሚጠየቁ ማብራሪያዎች ተገቢና ወቅታዊ ምላሽ ይሰጣል፡፡
- ከባለጉዳይ የሚቀርቡ ቅሬታዎችና አቤቱታዎችን በህጋዊ አሰራር መሰረት በጽሑፍ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፡፡
- በክላስተር ፅንስ ሐሳብ መሰረት ማደራጀት እንዲቻል ኢንተርፕራይዞችን በዘርፉ በያዙት የቦታ መጠን ይለያል፣ተግባራዊ እንዲሆን ያስተገብራል፡፡
- በተለያዩ አካላት የመስሪያ ቦታዎችን በሚመለከት የሚቀርቡ ጥቆማዎችን ተገቢውን የማጥራት ስራ በማድረግ አስፈላጊውን የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፣ ለኤጀንሲው ያሳውቃል፡፡
- ከኤጀንሲው ተወስነው የሚላኩ ጉዳዮችን በመመሪያው መሰረት ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
- በመስሪያ ቦታ የሚሰሩ አንቀሳቃሾችን ለማስተባበር የወጣ የግቢ ኮሚቴ ሞዴል መተዳደሪያ ደንብ ተግባራዊነቱን ክትትል ያደረጋል፡፡
- ከሌላ ክፍለ ከተማ በህጋዊ መንገድ ተደራጅተው የመስሪያ ቦታ እንዲሰጣቸው የተወሰነላቸውን ኢንተርፕራይዞችን ባለው ክፍት ቦታ እንዲመደቡ ያደርጋል፡፡
- ተገንብተው የተጠናቀቁና ለስራ ዝግጁ የሆኑ የመስሪያ ቦታዎችን ተደራሽ እንዲሆን ተደራጅቶ ለሚመጡ ኢንተርፕራይዞች ፍትህዊ በሆነ መልኩ በሚደባ ወይም ውድድር መስሪያ ቦታውን ያስተላልፊላቸዋል፡፡
- በመስሪያ ቦታ የቆይታ ጊዜያቸው አራት ዓመት የሞላቸው ኢንተርፕራይዞችን በመመሪያው መሰረት ቅድማ ዝግጅት እንዲያደርጉ የማሳወቂያ ደብዳቤ እንድሰጣቸው ያደርጋል፤ በየጊዜው ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል፡፡
- ወደ ታዳጊ መካከለኛ የዕድገት ደረጃ የተሸጋገሩትን ኢንተርፕራይዞች ተተኪ ቦታ ከተሰጣቸው የቆይታ ጊዜያቸውን ሳይጠብቁ የያዙትን የመስሪያ ቦታ እንዲለቁ በማድረግ ለኤጀንሲው ያሳውቃል፡፡
- ከመስሪያ ቦታ አሰጣጥ እና አጠቃቀም ጋር ተያይዞ የአሰራር ስርዓት ክፍተት ከተፈጠረ ከሚመለከተው አካል ጋር ጥናት በማድረግ ማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ ድጋፍ ያደርጋል፡፡
|
| | | | |