|
|
|
- የመስሪያ ቦታ ተጠቃሚ የሆኑ ኢንተርፕራይዞች የቆይታ ጊዜያቸው ውል ከገቡበት ቀን ጀምሮ ውሉ በየዓመቱ እየታደሰ የሚቆዩት ለ5 ዓመት ብቻ ነው፡፡
- የመስሪያ ቦታ ተጠቃሚዎች ሆነው ወደ መካከለኛ ኢንዱስትሪነት የተሸጋገሩ በተለይም በማምረት ስራ ላይ የተሰማሩትን በሚመለከት በዚህ መመሪያ አንቀጽ 15(2)ለ መሰረት የቆይታ ጊዜያቸው ሊራዘምላቸው ይችላል፡፡
- የኢኮኖሚ ሽግግር ማድረግ ያልቻሉና ከ5 አመት በላይ መስሪያ ቦታ ላይ የቆዩ አንቀሳቃሾች ወይም ኢንተርፕራያዞችን በሚመለከት በኤጀንሲው በኩል ልዩ ውሳኔ ካላገኙ በስተቀር በአንቀጽ 14(6) ላይ በተቀመጠው አግባብ የሚስተናገዱ ይሆናሉ፡፡
- በዚህ መመሪያ አንቀጽ 14(1)መ መሰረት ወደ ሥራ ያልገባ ኢንተርፕራይዝ ተጨማሪ የአንድ ወር ጊዜ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ወደ ሥራ ካልገባ ውሉ ተቋርጦ የመስሪያ ቦታውን በነበረበት እንዲያስረክብ ይደረጋል፡፡
|
| | | | |