የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ሥርዓት፡-
ኤጀንሲው ከተለያዩ የስራ ክፍሎች የተውጣጣ 5 አባልት ያሉት የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ያደራጃል፡፡
ከመስሪያ ቦታዎች አሰጣጥ፣ አጠቃቀምና አስተዳደር ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጉዳዮች ለቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ከመቅረባቸው በፊት በየደረጃ ባለው ለኤጀንሲው መዋቅር ቀርቦ በአጭር ጊዜ ውስጥ የመጫረሻ ውሳኔ ሊሰጥበት ይገባል፡፡
የመሥሪያ የቦታ ተጠቃሚዎች ከቦታው አሰጣጥ፣ አጠቃቀም እና አስተዳደር እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ቅሬታ ካለው ቅሬታውን በጹሁፍ ያቀርባል፣
ቅሬታ የቀረበለት የኤጀንሲው ክፍለ ከተማ ጽ/ቤት ጉዳዩን መርምሮ በሰባት የስራ ቀን ውስጥ በጹሁፍ ምላሽ መስጠት ይኖርበታል፡፡
በኤጀንሲው ክፍለ ከተማ ጽ/ቤት በተሰጠው ምላሽ ያልረካ ቅሬታ አቅራቢ የተሰጠውን ምላሽ አያይዞ በጽሑፍ በ5 የስራ ቀን ውስጥ ቅሬታውን ለኤጀንሲው ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ያቀርባል፡፡
የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴው የቀረበውን ቅሬታ መርምሮ ከውሳኔ ሃሳብ ጋር ቅሬታው ከቀረበበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ወይም እሱ ለሚወክለው አካል በጽሁፍ ያቀርባል፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ ወይም እሱ የሚወክለው አካል የቀረበለትን የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ውሳኔ ይሰጣል፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ ወይም እሱ በሚወክለው አካል ውሳኔ ያልረካ ቅሬታ አቅራቢ በጽሁፍ የሚሰጠውን ምላሽ ይዞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቅሬታ አቀራረብ መመሪያን ተከትሎ በቀጣይ ደረጃ ቅሬታውን ማቅረብ ይችላል፡፡
ለበለጠ መረጃ ይህን መመሪያ ቁ109/2014 ያንብቡ