በልደታ ክ/ከተማ የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት
የእንጨት፣ ብ/ብረትና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ቡድን

ግብ 1. በዘርፉ በየደረጃው የሚገኘው አመራርና ፈጻሚ አቅም በመገንባት መዋቅሩ እንዲጠናከርና የባለድርሻ አካለት ተሳትፎን በማጎልበት ተልዕኮውን በውጤታማነት እንዲወጣ ማድረግ

  • ተግባር 1. በ2016 በጀት አመት የከተማውን ዘርፍ መሪ ዕቅድ መሰረት በማድረግ ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ያሉ የቡድኖች እቅድ ኢንዲዘጋጅ ማድረግ፣
  • ተግባር 2. ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ለሚገኙ 25 የዘርፉ አመራሮች የእቅድ ኦረንቴሽን መስጠት፣
  • ተግባር 3. የዘርፉ አመራሮች በዘርፉ ተልዕኮ፣ ስትራቴጂና በአዲሱ መዋቅራዊ አደረጃጀት ላይ ስልጠና በመስጠት ስራቸውን በዕውቀት እንዲመሩ ማድረግ፡፡

ግብ 2፡- በየደረጃው የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች በመለየት ደረጃ በደረጃ እንዲፈቱ በማድረግ የዘርፉን አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሻሻል ተደርጓል፡፡

  • ተግባር 1. በዘርፉ በየደረጃው ያልተፈቱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለይቶ የአፈታት ስልቱን በሚያሳይ አግባብ ራሱን የቻለ ዕቅድ ማዘጋጀት፣
  • ተግባር 2. በዕቅዱ መሰረት ተግባራት እየተፈጸሙ መሆኑን በየጊዜው በአመራር እየተገመገመ እንዲሄድ ማድረግ፣
  • ተግባር 3. የተፈቱና ያልተፈቱትን ችግሮች እየለዩ በቀጣይነት ችግር እየፈቱ መሄድ፣

ግብ 3፡- በየደረጃው የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች በመለየት ደረጃ በደረጃ እንዲፈቱ በማድረግ እና የለውጥ ስራዎችን በተቀናጀ መልኩ በዘመናዊ አሠራር በማስደገፍ የዘርፉን አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻል

  • ተግባር 1. በዘርፉ የሚታየውን በአቋራጭና ያለአግባብ የመጠቀም ፍላጎቶችና ተግባራትን በተደራጀ ትግል እንዲዳከም ተደርጓል፣
  • ተግባር 2. በዘርፉ በየደረጃው ለብልሹ አሰራሮች ምቹ የሆኑ ሁኔታዎችን ለይቶ የማስተካከል ስራ በመስራት፣ የዘርፉ አመራርና ፈጻሚ ከሌብነት አስተሳሰብና ተግባር ነጻ ሆኖ ኢንዱስትሪዎቻችን ከዘርፉ የሚፈልጉትን አገልግሎት በአግባቡ መስጠት እንዲችል በተፈጠሩ አደረጃጀቶች የአመለካከት ቀረጻ ስራ አጠናክሮ መፈጸም፣
  • ተግባር 3.  በየደረጃው የሚዘጋጁና የሚላኩ ሪፖርቶች ተዓማኒና ከውሸት የጸዱ መሆናቸውን በክትትልና ድጋፍ እያረጋገጡ መሄድና ችግር ያለባቸውን አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረግ፣
  • ተግባር 4. በዘርፉ አንቀሳቀሾች ዘንድ የሚታየውን እላፊና ያለአግባብ የመጠቀምና ያልተገባ ድጋፍ የማግኘት አስተሳሰብና ተግባር ለማዳከም የሚያስችሉ የግንዛቤ መፍጠር ስራ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር እንዲለወጥ ማድረግ፣

ግብ 4. የለውጥ ስራዎችን በተቀናጀ መልኩ በዘመናዊ አሠራር አስደግፎ በመተግበር የህዝቡ እርካታና ተጠቃሚነት እንዲያድግ ተደርጓል፣

  • ተግባር 1.  በዘርፉ የለውጥ ስራዎች የሚመሩበት እራሱን የቻለ እቅድ ተዘጋጅቶ ተግባሩ በእቅድ እንዲመራና ወቅታዊ ግምገማ እየተደረገ እንዲሄድ ይደረጋል፣
  • ተግባር 2.  የሚዛናዊ ሥራ አመራርና ውጤት ተኮር ስርዓትን በተሻሻለው አደረጃጀት መሠረት በመከለስ ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ድረስ ለእያንዳንዱ የስራ ክፍልና ለእያንዳንዱ ፈፃሚ ተሸንሽኖ እንዲደርሰውና ተግባሩን በዛ አግባብ እንዲቃኝ ይደረጋል፣

ዓላማ አንድ ፡ - አምራች ኢንዱስትሪዎች የመሳሪያ ሊዝና የፋይናንስ ድጋፍ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ድጋፍ ማድረግ ፡፡

ግብ 1. ለ 50 ኢንዱስትሪዎች 6,930,000 የቅደመ ቁጠባና መደበኛ ቁጣባ እንዲቆጥቡ በማድረግ 33 አንዱስትሪዎች የ 16,283,988 ሚሊየን ብር የብድር አገልግሎት እንዲያገኙ እና ከተሰራጨው ብድር ዉስጥ 43 የሚሆኑት 2,970,000.00 ብር ከተዘዋዋሪና ከመደበኛ በአግባቡ እንዲመለስ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ፡፡

  • ተግባር 1. የብድር አገልግሎት ፍላጎት የላቸዉን ኢንዱስትሪዎች በደሳሰ ጥነት መለየት፣
  • ተግባር 2. አንድ ኢንዱስትሪዎች ብድር ለመውሰድ ማሟላት የሚገቡት መስፈርቶች ላይ ግንዛቤ የሚፈጥሩ መድረኮችን ማመቻቸት፣
  • ተግባር 3. ኢንዱስትሪዎች የወሰዱትን ብድር ለታለመለት አላማ እንዲያውሉ እና በወቅቱና በአግባቡ የወሰዱትን ብድር ተመላሽ እንዲያደርጉ አስፈላጊውን ግንዛቤ መፍጠርና ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣
  • ተግባር 4. በብድር አሰጣጥ ሂደቱ ላይ ያሉ ማነቆዎችን ከብድር አቅራቢው ተቋም ጋር በመቀናጀት እንዲፈቱ ማድረግ፣
  • ተግባር 5. ለመካከለኛ ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች የተሻሉ የብድር አማራጮችን ለማቅረብ እንዲቻል ከልማት ባንክና ከፌደራል የዘርፉ ባለድርሻዎች ጋር በትብብር መስራት

ግብ 2 ፡ የኢንዱስትሪዎች ምርትና ምርታማነታቸውን የሚያሳድግና ጥራት ያለው ምርት ማምረት እንዲችሉ ለ7 ኢንዱስትሪዎች የ17 መሠሪያ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ

  • ተግባር 1. አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ በሚሰራቸው ስራዎች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች ለኢንዱስትሪዎች እንዲዘጋጁ ማድረግ
  • ተግባር 2. በእንጨትና ብረታብረት ዘርፍ ያሉን ኢንዱስትሪዎች ዘመናዊና ምርትና ምርታማነታቸውን የሚያሳድጉላቸው ማሽኖችን በሊዝ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ፍላጎት መለየትና ግንዛቤ ማስጨበጥ፣
  • ተግባር 3. የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደገፍና የወሰዱትን ማሽን በአግባቡ እንዲጠቀሙና በሂደት ክፍያውን ፈጽመው የግላቸው እንዲያደርጉ አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣
ዓላማ 2. የእሴት ሰንሰለት ተከትሎ የክላስተር አደረጃጀት የአሰራር ስርዓቶችን በመዘርጋት ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ፡፡
ዓላማ 3. አዲስና ነባር የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ለተጠቃሚዎች ጥራቱን የጠበቀ ምርት በማቅረብ ቀጣይነታቸውን ማረጋገጥ፡፡

ግብ 3 ፡ ነባር 81 የማፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎችን የማጠናከርና የመደገፍ ስራ በመስራት የመክሰም ችግርን መቀነስና በተለይም አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ላይ በትኩረት በመስራት ነባሮቹ 215 ፤አዲስ የተቋቋሙ የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ---- አጠቃላይ ለ 215 ዜጎች የስራ ዕድል እንዲፈጠር ማድረግ፤

  • ተግባር 1. በዝግጅት ምዕራፍ ያጠራነውን የኢንዱስትሪዎች መረጃ የትንታኔ ሰነድ በማዘጋጀት ለሚመለከታቸው አካላት ተደራሽ ማድረግ፣
  • ተግባር 2. የኢንዱስትሪዎችን የመፍረስና የመክሰም ችግር ምንጩን በማጥናት 100% እንዲቀንስ መስራት፣
  • ተግባር 3. ከላይ ባሉ ግቦች የተዘረዘሩትን መንግስታዊ ድጋፎች ለሚገባቸው ኢንዱስትሪዎች በተገቢው መስጠትና ካላቸው ሰራተኛ በተጨማሪ የስራ ዕድል እንዲፈጥሩ ማበረታታት፣
  • ተግባር 4. በነባርና በአዲስ የተፈጠረውን የስራ ዕድል በየወቅቱ እያደራጁ ለስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ሪፖርት ማቅረብ

ግብ 5 ፡- 36 ለሚሆኑ ከእንጨትና ብረታብረት ኢንዱትሪዎች ምርትና ምርታማነትን እንዲያሳድጉ ሙያዊ ድጋፍ በማድረግ ለ38 ኢንዱስትሪዎች የምርታመነት ልኬት በማድረግ ----- ኢንዱስትሪዎች የመምረት አቅመቻዉ ከ57 ወደ 62 እንዲያድግ ማስቻል

  • ተግባር 1. የኢንዱስትሪ ልማት አቅጣጫዎችና የድጋፍ ማዕቀፎች ተግባራዊ እንዲሆኑ ድጋፍ ያደርጋል፤
  • ተግባር 2. በኢንደስትሪው ልማት ዘርፍ በጥናት የተገኙ ምርቶች ጥራታቸውን በጠበቀ መልኩ ተግባራዊ መሆናቸውን ይከታተላል፤ይቆጣጠራል፡
  • ተግባር 3. ኢንዱስትሪዎች ኤክስፖርትና ተኪ ምርት እንዲያመርቱ ከግብዓት እስከ ምርት ባለው ሂደት ቴክኒካል ድጋፍና ክትትል ማድረግ፤
  • ተግባር 4. በኢንደስትሪ ልማት ዘርፍ ምርቶችን በጥራት ለማምረት ተብሎ የተዘጋጁ ማንዋሎች በአግባቡ ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን መከታተል፤
  • ተግባር 5. ከሚመለከተው ተቋም ጋር በመሆን ምርታቸው እንዲመዘን ማድረግና ሂደቱን መከታተል፤በስታንዳርዱ መሰረት እንዲያመርቱ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤
  • ተግባር 6. የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎችን ምርትና ምርታማነት በመለካት ውጤታማነታቸው እንዲረጋገጥ ድጋፍ ማድረግ፤
  • ተግባር 7. በማምረት ሂደት ላይ በሚኖር የሙያና የአካባቢ ደህንነት አጠባበቅ ዙሪያ ላይ እንዲሰሩ ድጋፍ እና ክትትል ማድረግ፤የምርትና ምርታማነት መለከያ መስፈርት ያዘጋጃል፤
  • ተግባር 8. በተቀመጠው ልኬት መሰረት ለኢንዱስትሪዎች ግንዛቤ በመፍጠር ያሉበትን ደረጃ ያሳውቃል፤

ግብ 6 ፡ ከውጭ ሀገር ወደ ሃገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችን ተክተው የሚያመርቱ 11 ኢንተርፕራይዞችን ወደ 13 የማሳደግ በመስራት የገበያ ድጋፍ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ፡፡

  • ተግባር 1. ከውጪ ሀገር የሚገቡ ምርቶችን ተክተው በማምረት ላይ ያሉ ኢንዱስትሪዎችን ዝርዝር ሁኔታ በማጥናት በተለየ መልኩ እንዲደገፉና ውጤታማነታቸው ተጠናክሮ እንዲቀጥል በማድረግ ተሞክሮአቸው እንዲቀመር ማድረግ፣
  • ተግባር 2. የተቀመረውን ተሞክሮ የተሻለ ብቃት ላይ ላሉ ኢንዱስትሪዎች እንዲሰፋ በማድረግ ኢምፖርት መተካት ላይ ያተኮሩ ምርቶች ማምረት እንዲጀምሩ ተገቢ ድጋፍ ማድረግ፣
  • ተግባር 3. ለሚያመርቱት ምርት በልዩ ሁኔታ የገበያ ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ ማድረግ፣
  • ተግባር 4. ምርቶቻቸውን ኤክስፖርት በማድረግ ላይ ያሉ ኢንዱስትሪዎች በመለየት ያሉበትን ሁኔታ በማጥናት በልዩ ሁኔታ ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ፣
  • ተግባር 5. ወደ ኤክስፖርት ስራ መግባት የሚችሉ ኢንዱስትሪዎችን በመለየትና በልዩ ሁኔታ በመደገፍ ገበያውን እንዲቀላቀሉ ተገቢ ድጋፍ ማድረግ፣
  • ተግባር 6. የምርት ደረጃ ሰርትፊኬት ያገኙ ኢንዱስትሪዎች የውጭ ገበያ እንዲያገኙ መረጃውን ለሚመለከተው ክፍል ማስተላለፍ፤

ግብ 7 ፡ 10 ለሚሆኑ ከማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ውጭ ላሉ የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች እና የህብረተሰብ ክፍሎች የዘርፉን ልማት ግንዛቤ ማሳደግ፡፡

  • ተግባር 1. ከዘርፉ ውጭ ላሉ ባለሃብቶች የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ያሉ ምቹ ሁኔታዎች ላይ ግንዛቤ መፍጠር፤
  • ተግባር 2. በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስደትሪ ዘርፍ ልማት ላይ ያሉ መንግስታዊ ድጋፎች ላይ ግንዛቤ መፍጠር፤
  • ተግባር 3. ከዘርደፉ ውጭ ያሉ ባለሃብቶች በዘርፉ ለመደራጀት እንደ ተግዳሮቶች የሆነባቸውን ሁኔታዎች በመተንተን የሚፈቱበትን መንገድ ማመቻቸት፤
  • ተግባር 4. የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች፣ የዩኒቨርስቲ ምሩቃን እና ከዘርፉ ውጭ ላይ ለተሰማሩ ዜጎች የኢንቨስትመንትና ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ፕሮሞሽን ስራዎችን መስራት፣
  • ተግባር 5. ወደ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለመሰማራት ለሚፈልጉ ባለሃቶች ወይም ስራ ፈላጊዎች ግንዛቤ መፍጠር፤
ዓላማ አራት ፡ ፍላጎትና ክፍተትን መሰረት ያደረገ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማመቻቸት ብቁ ማድረግ ፡፡

ግብ 8 ፡- የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎችን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ፍላጎትንና ክፍተትን መሰረት ባደረገ መልኩ ድጋፉ ለሚገባቸው 59 ነባርና 35 አዲስ በድምሩ 94 ኢንዱስትሪዎችን በመለየት የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ፓኬጅ ድጋፎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆች በማስረከብ የድጋፍ ስራውን ማስጀመር

  • ተግባር 1. የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ እንዲደረግላቸው ፍላጎት ከተለየው100 ኢንተርፕራይዞች መካከል ድጋፉ የሚያስፈልጋቸውን 94 ኢንዱስትሪዎች በማጥራት ፍላጎትንና ክፍተትን መሰረት ባደረገ መልኩ በድጋሚ በመለየት ዝርዝራቸውን ለቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ማስረከብ፣
  • ተግባር 2. ኢንተርፕራይዞቹ በተመደቡበት የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ተገቢውን ድጋፍ እያገኙ መሆኑን መከታተል፣ ጉድለቶች ሲኖሩ ከኤጀንሲው አመራር ጋር በመገምገም እንዲታረሙና የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ስራው ውጤታማ እንዲሆን አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግና በድጋፉ ያመጡትን ውጤት መመዘን፣
  • ተግባር 3. በተሰጣቸው የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ መሰረት ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ማስቻል፤
  • ተግባር 4. የካይዘን ስልጠና የወሰዱ ኢንተርፕራይዞች በካይዘን ጽንሰ ሀሳብ መሰረት ተግባራዊ እንዲያደርጉ ተከታታይ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፤

ግብ 9 ፡ ለማኑፋክቸሪንግ ኢንዱትሪዎች ችግር ፈቺና አዋጭ የሆኑ ከተኮረጁና ከተሻሻሉ 1 ቴክኖሎጂዎች ውስጥ 1 የሚሆኑትን ለ 1 ኢንዱስትሪዎች በማሸጋገር ድጋፍ በማድረግ ምርታማነታቸውን ማሳደግ

  • ተግባር 1. በመስኩ በቴክኖሎጂና ግብዓትና የአመራረት ሂደቱን አጠቃቀም ዙሪያ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ሙያዊ ድጋፍ ይደርጋል፣
  • ተግባር 2. በተቋማትና በራሳቸው በኢንዱስትሪዎች የተሰሩ ቴክኖሎጂዎችን ለኢንዱስትሪዎቹ እንዲሸጋገሩ ማመቻቸት፤
  • ተግባር 3. የተረጋገጠውን ምርጥ ቴክኖሎጂ ከቴክኒክና ሙያ ተቋማት ጋር በመተባበር ለጥቃቅን፣ አንሰተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ያሸጋግራል፤
  • ተግባር 4. የማፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች በራሳቸው የሚያመርቷቸውን ወይም የሚጠቀሟቸውን ቴክኖሎጂዎች በመለየት የባለቤትነት ማረጋገጫ (patent right) እንዲያገኙ እና እንዲሰፋ የማድረግ ስራ ይሰራል፤

ግብ 10 ፡- ለ 20 በማኑፋክቸሪን ዘርፍ የተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚረዳ ፍላጎትንና ክፍተትን መሰረት ባደረገ መልኩ የክህሎትና የቴክኒክ ስልጠና ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆችና ጋር በመቀናጀት ማሰልጠንና አቅም መገንባት ፡፡

  • ተግባር 1. በእጩ ሞዴልና በሞዴልነት የተለዩት እንዲሁም ኢምፖርት በመተካትና ኤክስፖርት በማድረግ ስራ ላይ የተሰማሩነንት ኢንዱስትሪዎችን በመለየት በክህሎትና በቴክኒክ በኩል ያለባቸውን ክፍተት መለየት፣
  • ተግባር 2. ከኢንዱስትሪዎቹ የስልጠና ፍላጎት ዳሰሳ መለየትና በምን ጉዳይ ላይ ስልጠና ማግኘት እንደሚፈልጉ መገንዘብ፣
  • ተግባር 3. ክፍተቱን መሙላት የሚያስችል ስልጠና ለመስጠት የሚያስችል ራሱን የቻለ ማስፈፀሚያ እቅድና የድርጊት መርሀ-ግብር ማዘጋጀት፣
  • ተግባር 4. ስልጠናውን ማደራጀትና መስጠት ቀጥሎም ስልጠናው የፈጠረውን አቅምና ያመጣውን ውጤት በመገምገም ለቀጣይ ስራ በግብኣትነት መጠቀም
  • ተግባር 5. የቴክኒካል ክህሎት ክፍተት ልየታ በዓይነትና በይዘት ሊገልጽ በሚችል መልኩ የዳሰሳ ጥናት ሰነድ ማዘጋጀትና መተንተን፤

  • በክ/ከተማ አስተዳደሩ ለጽ/ቤቱ የተሰጠው ክብደት ከፍተኛ መሆኑ በም/ዋና ስራ አስፈጻሚ በቀጥታ እንዲመራ መደረጉና ተናባቢነት ያለውን መዋቅራዊ አደረጃጀት መፍጠሩና ሊያሠራ የሚችል የትምህርት ዝግጅት፣ የተለያየ ልምድ ያለው የሰው ኃይል መኖሩ፤

  • ጽ/ቤቱ በተሻለ አቅም መልሶ መደራጀቱ ለጽ/ቤቱ ሥራ ማስፈጸሚያ የሚመደበው በጀት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱና የጽ/ቤቱ በጀት አጠቃቀሙ እየተሻሻለ መምጣቱ፤

  • የኃይል አቅርቦት መሻሻል ለኢንዱስትሪ መስፋፋት በጎ አስተዋጽዖ እያደረገ መሆኑ፤

  • የምርምርና ስርፀት ተቋማት እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መስፋፋት፣

  • አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የመጠቀም ፍላጎትና አቅም እያደገ መምጣቱ፤ በሀገራችን የዲጂታል ማርኬትንግ እየተስፋፋ መምጣቱ፣
የአፈፃጸም አቅጣጫ

  1. የምናከናውናቸውን ተግባራት ተቋማዊ በሆነና የተፈጠሩ የዘርፉ አደረጃጀቶችን በቀጣይነት ወደ ተጨባጭ ተግባር በማስገባት የመፈፀም አቅማችንን ማጎልበት እንደ ዋነኛ አቅጣጫ ይዘን እንሰራለን፣

  2. በቴክኖሎጂ የተደገፈና የአገልግሎት አሰጣጡን ግልጽ ቀልጣፋና ወጪ ቆጣቢ በማድረግ የኢንዱስትሪዎችን የአገልግሎት ፍላጎት በማርካት መልካም አስተዳደርን በሚያሰፍን ሁኔታ በትጋት ይሰራል፣

  3. ተግባሮቻችን በሙሉ ልማታዊ አስተሳሰብን በሚያጎለብትና ሌብነትን በሚያዳክም መንገድ እንዲፈጸሙ የማድረግ አቅጣጫን አንከተላለን፡፡

  4. ተግባሮቻችን አሳታፊ፣ ግልጽና ተጠያቂነት በሚያሰፍን መልኩ እንዲፈጸሙና የህዝብ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ አቅጣጫ እንዲፈጽሙ እንሰራለን፡፡

  5. ተግባሮቻችን በሙሉ በባለድርሻ አካላትና በሚመለከታቸው ተቋማት ቅንጅት እንዲፈጽሙ የማድረግ አቅጣጫን እንከተላለን፡፡