|
|
አዲስ የመስሪያ ቦታ ጥያቄ ለሚያቀርቡ የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ሟሟላት የሚገባቸው ጉዳዮች፣
|
|
- የሚመለመሉ ኢንተርፕራይዞች ኤጀንሲው ከሚያስተዳድረው የመሥሪያ የቦታ መጠንና የዘርፍ አይነት ጋር የተመጣጠነ ሲሆን፣
- ከቢሮ እና አስከ ወረዳ ባሉ የቢሮ መዋቅር ተመልምለው ወደ ኤጀንሲው የሚመጡ ኢንተርፕራይዞች የመስሪያ ቦታ ድጋፍ እንዲደረግላቸው የተወሰነበት ቃለ ጉባኤ ከነአስፈላጊ የአደረጃጀት ሰነዶች ጋር መቅረብ ሲችል፣
- የጥቃቅን ወይም አነስተኛ ወይም የመካከለኛ ኢንትርፕራይዝ የዕድገት ደረጃ ማረጋገጫ ሲያቀርብ፣
- ለአዲስ ኢንተርፕራይዝ አዋጭ ቢዝነስ ፕላን ሲያቀርብ፣
- የከተማ የነዋሪነት መታወቂያ፣
|
ለመሸጫና ማምረቻ ዘርፍ አገልግሎት የሚውል ህንፃ ላይ የመስሪያ ቦታ አሰጣጥን በተመለከተ፡-
- ለህንፃው ደህንነት ሲባል በሚቀርቡት የማምረቻ መሳሪያዎች እና ዕቃዎች ክብደትና የስራው ባህሪ የቦታ ምደባው በኤጀንሲው የሚወሰን ሆኖ በአንቀጽ 8(1-4) የተጠቀሱት ምርትና አገልግሎቶች የሚገቡ ይሆናል፡፡
- በመሸጫ ህንጻ ላይ ለኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ፣ ለኢንተርኔትና ኮምፒውተር ጥገና አገልግሎቶች 3ኛ ወለል ላይ የሚሰጥ ሲሆን የሚከተሉት የስራ መስኮች በምድር እና በአንደኛ ወለል የሚደለደሉ ይሆናል፡፡
- በዘርፉ ስራ ላይ የተሰማሩ አካል ጉዳተኞች እና መውጣትና መውረድ እንደማይችሉ በህክምና ማስረጃ የተረጋገጠላቸው ህሙማን፤
- የአትክልትና ፍራፍሬ፣ ካፌና ሬስቶራንትና የእንስሳት ተዋጽኦ፤
- የእንጨትና ብረታ ብረት ውጤቶችና የኮንስትራክሽን ውጤቶች
- ሌሎች ተጠቃሚዎች በየትኛውም ቦታ ሊመደቡ ይችላሉ፡፡
- የገበያ ማዕከል (ኢንፖሪየም) ማሳያን በተመለከተ በቀጣይ በሚገነቡ ማዕከላት ኤጅንሲው በሚያወጣው የቦታ አጠቃቀም ማሰፈጸሚያ ሰነድ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
| | | | | | |