ዓላማ 1. ተቋማዊ ሪፎርም ከሰው ሃይል፣ከቴክኖልጂ እና ከመመሪያ ዝግጅት ያለውን ክፍተት በማስተካከልና በመተግበር አመራሩና ሰራተኛው የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ፈጥሮ የተሰጠውን ኃላፊነት መወጣት የሚያስችል ቁመና ላይ ማድረስ፡፡
- ተግባር 1. በሰው ሀይል ልማታችን አዲስ የተጠናውን መሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ (BPR) አደረጃጀት በመተግበር መዋቅራዊ ቁመናን ማጠናከርና እስከ ወረዳ ድረስ ምደባውን በማከናወን የተናበበና ተልእኮ ማስፈፀም የሚያስችል ደረጃ ላይ ማድረስ፣
- ተግባር 2. አዲስ የተጠናውን መሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ (BPR) ማስፈፀም በሚችል መልኩ የጽ/ቤቱን መመሪያ፣ ማኑዋልና አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግ ለተቋማዊ ለውጥና አሰራር የማያመቹትን ለይቶ እንዲስተካከሉ ማድረግ፣
- ተግባር 3. ጽ/ቤቱ ስራውን ለማቀላጠፍ የሚያግዘ ነባሮቹን ቴክኖሎጂዎችን በማዘመንና አዲስ መልማት የሚገባቸውን በማልማት የተቋሙን አገልግሎት ማቀላጠፍ፡፡
አላማ 2፡- በዘርፉ የሰው ሃይል 70 በመቶ በማሟላት በተዘጋጁ መመሪያዎች፣ ማኑዋልች፣ ስትራቴጂዎችና ልዩ ልዩ የክህሎት ስልጠናዋዎችን በመስጠትና አቅም በመገንባት መዋቅሩ እንዲጠናከርና በውጤታማነት እንዲወጣ ማድረግ
- ተግባር 1. የቡድኑን የ2016 ዓ.ም እቅድ ከጽ/ቤቱ እንዲሁም እስከ ከተማ መዋቅር እንዲናበብ ማድረግ፣
- ተግባር 2. የተዘጋጁትን ዕቅዶች አንድ ደረጃ ከፍ ብሎ የሚገኘው አካል ገምግሞ ግብረ መልስ እንዲሰጥ ማድረግ፣
- ተግባር 3. በዘርፉ የሰው ሃይል 70 በመቶ በማሟላት የዘርፉ ተልእኮ እንዲሳካ ማድረግ፣
- ተግባር 4. የዘርፉ ፈጻሚዎችን በተዘጋጁ መመሪያዎች፣ማኑዋልች፣ስትራቴጂዎችና ልዩ ልዩ የክህሎት ስልጠናዎችን በመስጠትና አቅም በመገንባት መዋቅሩ እንዲጠናከርና ተልዕኮውን በውጤታማነት እንዲወጣ ማድረግ፣
አላማ 3፡- በየደረጃው የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች በመለየት ደረጃ በደረጃ እንዲፈቱ በማድረግ እና የለውጥ ስራዎችን በተቀናጀ መልኩ በዘመናዊ አሠራር በማስደገፍ የዘርፉን አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻል
- ተግባር 1. በዘርፉ በየደረጃው ያልተፈቱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለይቶ የአፈታት ስሌቱን በሚያሳይ አግባብ ራሱን የቻለ ዕቅድ ማዘጋጀት፣
- ተግባር 2. የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በአግባቡ በመለየት 100% እየተፈቱ መሆኑን ለማረጋገጥ በየጊዜው በአመራር እየተገመገመ እንዲኬድ ማድረግ፣
- ተግባር 3. በየደረጃው ሁለም ስራዎች በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት እየተፈጸሙ መሆኑን ማረጋገጥና ከስታንዳርድ በላይ፣ በስታንዳርድና ከስታንዳርድ በታች የሚፈፅሙ አገልግሎቶች በየስራ ክፍሎችና ባለሙያዎች እየተለዩ እንዲተገበሩ ማድረግ፣
- ተግባር 4. የስራ አፈፃፀም ጥራትና የውጤት ምዘና ሂደት ላይ ግልፅ አሰራር በመዘርጋት በአዲሱ አውቶሜሽን መሰረት 2 ጊዜ ምዘና በማካሄድ፣
- ተግባር 5. የዘርፉን አገልግሎት አሰጣጥ በማሻሻል የተገልጋዩን እርካታ አሁን ካለበት 60% ማድረስ፣
ዓላማ 4. በዘርፉ የሚታየውን በአቋራጭና ያለአግባብ የመጠቀም ፍላጎቶችና ተግባራትን በተደራጀ ትግል እንዲዳከምና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ማድረግ ተችሏል፡፡
- ተግባር 1. ለብሌሹ አሰራሮች ምቹ የሆኑ ዘርፍችን በመለየት ችግሩ የሚገለጽበትን ዘርፍ በዳሰሳ ጥናት በመለየትና የማክሰሚያ ምንጩንም በማቀድ፤የማስተካከያና አሰራሩን የማዘመን ስራ መስራት፣
- ተግባር 2. የዘርፉ አመራርና ፈጻሚ ከሌብነት አስተሳሰብና ተግባር ነጻ እንዲሆን ተቋማዊ እሴቶችን ማስረፅና ሙያዊ ስነ-ምግባር እንዲሊበስ 2 የአመለካከት ቀረጻ መድረክ ማዘጋጀት፣
- ተግባር 3. በየደረጃው የሚዘጋጁና የሚላኩ ሪፖርቶች ተዓማኒና ከውሸት የጸዱ መሆናቸውን በየሩብ አመቱ በክትትልና ድጋፍ እያረጋገጡ መሄድና ችግር ያለባቸውን አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረግ፣
- ተግባር 4. በዘርፉ የሚስተዋሉ የሌብነትና እላፊ ተጠቃሚነት አስተሳሰቦችንና ተግባራትን ለማዳከም የባለድርሻ አካላት ሚናቸውን እንዲወጡ የሚያስችል ስራ መስራት፣ የተጠያቂነት ስርአት መዘርጋት፣
አላማ 5 ፡- የዘርፉ የልማት ስራዎችን በየደረጃው በሚገኙ በህብረተሰብ ክፍሎች ግንዛቤ ለማስጨበጥ በ4 የተለያዬ የኮሙኒኬሽን አግባቦች 2 የተለያዩ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ በማድረስ አዎንታዊ አመለካከትን መፍጠር፡
- ተግባር 1. የህዝብ ግንኙነት ስራው እራሱን በቻለ እቅድ ተዘጋጅቶለት በተደራጀ መልኩ እንዲመራ ማድረግ፣
- ተግባር 2. የተዘጋጀና የተሰራጨ የህትመት ውጤት 1 ፍላየር፣ 1 ብሮሸር እንዲሁም በተለያዩ ርእሰ 100 ኮፒ ማሰራጨት፣