በልደታ ክ/ከተማ የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት
የኢንዱስትሪ ሠላምና የሙያ ደህንነት ቡድን

ግብ 1. በመልካም አስተዳደርና በአገልግሎት አሰጣጥ ግልጸኝነ እና ተጠያቂነትን በማስፈን የህዝቡን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ

ዓላማ 1. ተቋማዊ ሪፎርም ከሰው ሃይል፣ከቴክኖልጂ እና ከመመሪያ ዝግጅት ያለውን ክፍተት በማስተካከልና በመተግበር አመራሩና ሰራተኛው የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ፈጥሮ የተሰጠውን ኃላፊነት መወጣት የሚያስችል ቁመና ላይ ማድረስ፡፡

  • ተግባር 1. በሰው ሀይል ልማታችን አዲስ የተጠናውን መሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ (BPR) አደረጃጀት በመተግበር መዋቅራዊ ቁመናን ማጠናከርና እስከ ወረዳ ድረስ ምደባውን በማከናወን የተናበበና ተልእኮ ማስፈፀም የሚያስችል ደረጃ ላይ ማድረስ፣
  • ተግባር 2. አዲስ የተጠናውን መሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ (BPR) ማስፈፀም በሚችል መልኩ የጽ/ቤቱን መመሪያ፣ ማኑዋልና አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግ ለተቋማዊ ለውጥና አሰራር የማያመቹትን ለይቶ እንዲስተካከሉ ማድረግ፣
  • ተግባር 3. ጽ/ቤቱ ስራውን ለማቀላጠፍ የሚያግዘ ነባሮቹን ቴክኖሎጂዎችን በማዘመንና አዲስ መልማት የሚገባቸውን በማልማት የተቋሙን አገልግሎት ማቀላጠፍ፡፡

አላማ 2፡- በዘርፉ የሰው ሃይል 70 በመቶ በማሟላት በተዘጋጁ መመሪያዎች፣ ማኑዋልች፣ ስትራቴጂዎችና ልዩ ልዩ የክህሎት ስልጠናዋዎችን በመስጠትና አቅም በመገንባት መዋቅሩ እንዲጠናከርና በውጤታማነት እንዲወጣ ማድረግ

  • ተግባር 1. የቡድኑን የ2016 ዓ.ም እቅድ ከጽ/ቤቱ እንዲሁም እስከ ከተማ መዋቅር እንዲናበብ ማድረግ፣
  • ተግባር 2. የተዘጋጁትን ዕቅዶች አንድ ደረጃ ከፍ ብሎ የሚገኘው አካል ገምግሞ ግብረ መልስ እንዲሰጥ ማድረግ፣
  • ተግባር 3. በዘርፉ የሰው ሃይል 70 በመቶ በማሟላት የዘርፉ ተልእኮ እንዲሳካ ማድረግ፣
  • ተግባር 4. የዘርፉ ፈጻሚዎችን በተዘጋጁ መመሪያዎች፣ማኑዋልች፣ስትራቴጂዎችና ልዩ ልዩ የክህሎት ስልጠናዎችን በመስጠትና አቅም በመገንባት መዋቅሩ እንዲጠናከርና ተልዕኮውን በውጤታማነት እንዲወጣ ማድረግ፣

አላማ 3፡- በየደረጃው የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች በመለየት ደረጃ በደረጃ እንዲፈቱ በማድረግ እና የለውጥ ስራዎችን በተቀናጀ መልኩ በዘመናዊ አሠራር በማስደገፍ የዘርፉን አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻል

  • ተግባር 1. በዘርፉ በየደረጃው ያልተፈቱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለይቶ የአፈታት ስሌቱን በሚያሳይ አግባብ ራሱን የቻለ ዕቅድ ማዘጋጀት፣
  • ተግባር 2. የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በአግባቡ በመለየት 100% እየተፈቱ መሆኑን ለማረጋገጥ በየጊዜው በአመራር እየተገመገመ እንዲኬድ ማድረግ፣
  • ተግባር 3. በየደረጃው ሁለም ስራዎች በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት እየተፈጸሙ መሆኑን ማረጋገጥና ከስታንዳርድ በላይ፣ በስታንዳርድና ከስታንዳርድ በታች የሚፈፅሙ አገልግሎቶች በየስራ ክፍሎችና ባለሙያዎች እየተለዩ እንዲተገበሩ ማድረግ፣
  • ተግባር 4. የስራ አፈፃፀም ጥራትና የውጤት ምዘና ሂደት ላይ ግልፅ አሰራር በመዘርጋት በአዲሱ አውቶሜሽን መሰረት 2 ጊዜ ምዘና በማካሄድ፣
  • ተግባር 5. የዘርፉን አገልግሎት አሰጣጥ በማሻሻል የተገልጋዩን እርካታ አሁን ካለበት 60% ማድረስ፣
ግብ 2. የሌብነትና ብልሹ አሰራር ላይ ሁሉን አቀፍ ትግል ማድረግ የሚያስችል ስርዓት በመዘርጋት ተጠያቂነትን ማረጋገጥ እና የኮሙኒዩኬሽን ስራዎችን ማጠናከር፣

ዓላማ 4. በዘርፉ የሚታየውን በአቋራጭና ያለአግባብ የመጠቀም ፍላጎቶችና ተግባራትን በተደራጀ ትግል እንዲዳከምና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ማድረግ ተችሏል፡፡

  • ተግባር 1. ለብሌሹ አሰራሮች ምቹ የሆኑ ዘርፍችን በመለየት ችግሩ የሚገለጽበትን ዘርፍ በዳሰሳ ጥናት በመለየትና የማክሰሚያ ምንጩንም በማቀድ፤የማስተካከያና አሰራሩን የማዘመን ስራ መስራት፣
  • ተግባር 2. የዘርፉ አመራርና ፈጻሚ ከሌብነት አስተሳሰብና ተግባር ነጻ እንዲሆን ተቋማዊ እሴቶችን ማስረፅና ሙያዊ ስነ-ምግባር እንዲሊበስ 2 የአመለካከት ቀረጻ መድረክ ማዘጋጀት፣
  • ተግባር 3. በየደረጃው የሚዘጋጁና የሚላኩ ሪፖርቶች ተዓማኒና ከውሸት የጸዱ መሆናቸውን በየሩብ አመቱ በክትትልና ድጋፍ እያረጋገጡ መሄድና ችግር ያለባቸውን አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረግ፣
  • ተግባር 4. በዘርፉ የሚስተዋሉ የሌብነትና እላፊ ተጠቃሚነት አስተሳሰቦችንና ተግባራትን ለማዳከም የባለድርሻ አካላት ሚናቸውን እንዲወጡ የሚያስችል ስራ መስራት፣ የተጠያቂነት ስርአት መዘርጋት፣

አላማ 5 ፡- የዘርፉ የልማት ስራዎችን በየደረጃው በሚገኙ በህብረተሰብ ክፍሎች ግንዛቤ ለማስጨበጥ በ4 የተለያዬ የኮሙኒኬሽን አግባቦች 2 የተለያዩ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ በማድረስ አዎንታዊ አመለካከትን መፍጠር፡

  • ተግባር 1. የህዝብ ግንኙነት ስራው እራሱን በቻለ እቅድ ተዘጋጅቶለት በተደራጀ መልኩ እንዲመራ ማድረግ፣
  • ተግባር 2. የተዘጋጀና የተሰራጨ የህትመት ውጤት 1 ፍላየር፣ 1 ብሮሸር እንዲሁም በተለያዩ ርእሰ 100 ኮፒ ማሰራጨት፣

ግብ 1. ለአምራች ኢንዱስትሪዎችና ለኢንተርፕራይዞች የሚውል ክላስተር ማዕከላት እና የመስሪያ ቦታዎችን በማልማትና በማስተዳደር የሀገር አኮኖሚ ማሳደግ፤

ዓላማ 1. የ4 ነባር ህንፃዎች እና 11 ሼዶች የጉዳት መጠን በጥናት በመለየት ጥገና ማድረግ፡፡

  • ተግባር 1. የጥገና ሥራውን ለማከናወን የሚያስችል በጀት መያዙን ማረጋገጥ በጀት ካልተያዘ እንዲያዝ ክትትል ማድረግ፣
  • ተግባር 2. ዕድሳትና ጥገና የሚያስፈልጋቸው 4 ህንጻዎች እና የ11 ሼዶችን ጉዳት በዝርዝር እንዲለይ ማድረግ፣
  • ተግባር 3. የህንጻና ሼዶች ጥገና ስራ ማከናወን፡፡

አላማ 2፡- በክፍለ ከተማ 12 አዲስ የሚገነቡ ሱቆች ግንባታቸው እንዲጠናቀቅ ክትትል ማድረግ

  • ተግባር 1. አዳዲስ ግንባታ ለማስጀመር የሚሆን በጀት መያዙን ማረጋገጥ፣
  • ተግባር 2. በክፍለ ከተማ 7 አዲስ የሚገነቡ ሼዶች ግንባታቸው እንዲጠናቀቅ ክትትል ማድረግ
  • ተግባር 3. ግንባታቸው የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን ርክክብ መፈጸም፣
ግብ 2. የባለ- ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች በቅንጅት ማጎልበት

ዓላማ 1. የዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን በማከናወን ተቋሙ የተሻለ የመፈፀም ብቃት እንዲኖረው ማድረግ፡፡

  • ተግባር 1. በኤች ኤይ ቪ ኤዲስ ላይ ያለውን ግንዛቤ ለማዳበር 2 መድረክ በማዘጋጀት በመንግስት መዋቅራችን የተጠናከረ ስራ መስራት፣ ማድረግ፤
  • ተግባር 2. የመረጃ አያያዝ ስርዓትን በማዘመን የሰዉ ሀብት ልማት ማሻሻል፡

አላማ 4 ፡- የሰው ሃብት ልማትን በማሳደግ ውጤታማ የሃብት አስተዳደርና አጠቃቀም ስርአትን መዘርጋት፣

  • ተግባር 1. የሰዉ ሀብት አስተዳደሩን በመረጃ ቋት ውስጥ ዘመናዊ ለማድረግ በተቀናጀ ኢንፎርሜሽን ሲስተም በማደራጀት የቡድኑን ሰራተኞችን መረጃ በመረጃ ቋት ዉስጥ እንዲገባ ማድረግ፣
  • ተግባር 2. የሰው ሃብት ጊዜ አጠቃቀም ውጤታማነት 70 በመቶ ማድረስ፣

አላማ 5፡- የመንግስት የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ስርዓቱን በማጠናከር ውጤታማ በሆነ አግባብ በቁጠባና ከብክነት እንዲፀዳ ማድረግ፡፡

  • ተግባር 1. የመንግስት ንብረት በተገቢው መያዝን በስራ ክፍላችን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ
  • ተግባር 2. በበጀት አመቱ ለመደበኛና ለካፒታል የተፈቀደውን (የፀጸቀ) በጀት በወጪ በጀት በአስተዳደሩ የፋይናንስ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ መሠረት 100% ጥቅም ላይ በማዋል ክፍያ እንዲፈጸም ማድረግ፣
  • ተግባር 3. የመንግስት ዕቃና አገልግሎት ግዢ በግዢ ደንብና መመሪያ መሰረት በመፈጸም ከሌብነትና ብልሹ አሰራር የጸዳ እንዲሆን ለማድረግ ግዣች በግልጽ ጨረታ እንዲፈጸሙ ወቅቱን ጠብቆ ጥያቄ ማቅረብ፣
  • ተግባር 4. የግዢ፣ የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ተግባሮች በተቀመጠላቸው የአሰራር ስርዓት መሰረት መከናወናቸውን 4 ጊዜ በአይቤክስ ሪፖርት በማረጋገጥ የሚታዩ ችግሮችን ማረምና ተጠያቂነትን ማስፈን፣

  • በክ/ከተማ አስተዳደሩ ለጽ/ቤቱ የተሰጠው ክብደት ከፍተኛ መሆኑ በም/ዋና ስራ አስፈጻሚ በቀጥታ እንዲመራ መደረጉና ተናባቢነት ያለውን መዋቅራዊ አደረጃጀት መፍጠሩና ሊያሠራ የሚችል የትምህርት ዝግጅት፣ የተለያየ ልምድ ያለው የሰው ኃይል መኖሩ፤

  • ጽ/ቤቱ በተሻለ አቅም መልሶ መደራጀቱ ለጽ/ቤቱ ሥራ ማስፈጸሚያ የሚመደበው በጀት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱና የጽ/ቤቱ በጀት አጠቃቀሙ እየተሻሻለ መምጣቱ፤

  • የኃይል አቅርቦት መሻሻል ለኢንዱስትሪ መስፋፋት በጎ አስተዋጽዖ እያደረገ መሆኑ፤

  • የምርምርና ስርፀት ተቋማት እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መስፋፋት፣

  • አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የመጠቀም ፍላጎትና አቅም እያደገ መምጣቱ፤ በሀገራችን የዲጂታል ማርኬትንግ እየተስፋፋ መምጣቱ፣